Established in 2023, the Amhara Mahber of Arizona is a community-driven non-profit organization dedicated to providing essential humanitarian aid and sustainable support to internally displaced Amhara people in Ethiopia affected by natural and manmade disasters. By mobilizing the resources and professional expertise of the diaspora in Arizona, the association focuses on delivering life-saving relief, advocating for the fundamental human rights of vulnerable populations, and fostering strategic collaborations with international NGOs and human rights organizations. Through its commitment to solidarity and cultural heritage, the Mahber serves as a vital bridge between the Arizona community and those in crisis, working tirelessly to restore dignity, ensure safety, and empower displaced families to rebuild their lives and achieve long-term resilience.
በ2023 እ.ኤ.አ. የተመሰረተው በአሪዞና የአማራ ማህበር፣ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች አስፈላጊ ሰብአዊ እርዳታ እና ዘላቂ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመ የማህበረሰብ ረድኤት ድርጅት ነው። ማህበሩ በአሪዞና የሚገኘውን የዳያስፖራ አባላት አቅም እና ሙያዊ እውቀት በማስተባበር፣ አስቸኳይ የህይወት አድን እርዳታዎችን ማቅረብ ላይ ያተኩራል። በተጨማሪም፣ ከተጋላጭ ወገኖች ጎን በመቆም ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሚሟገት ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጋር ስትራቴጂካዊ ትብብር ይፈጥራል። ማህበሩ የአማራን ባህላዊ እሴቶች እና አንድነትን መሰረት በማድረግ፣ በአሪዞና ማህበረሰብ እና በችግር ውስጥ ባሉ ወገኖች መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል፤ ተፈናቃይ ቤተሰቦች ሰብአዊ ክብራቸው ተጠብቆ ህይወታቸውን መልሰው እንዲገነቡ እና ዘላቂ ጥንካሬ እንዲያገኙ በትጋት ይሰራል፡፡
Mission Statement
To provide life-saving assistance and sustainable support to internally displaced Amhara people in Ethiopia by mobilizing resources within Arizona, advocating for human rights, and fostering strategic partnerships with global humanitarian organizations to restore dignity and stability.
በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈናቀሉ የአማራ ተፈናቃዮች፣ በአሪዞና የሚገኙ ሀብቶችን በማሰባሰብ፣ ሰብአዊ መብቶችን በመሟገት እና ከዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በመፍጠር፣ አስቸኳይ የህይወት አድን እርዳታ እና ዘላቂ ድጋፍ መስጠት።
Vision Statement
A future where every displaced Amhara individual is empowered to rebuild their life in a safe, just, and resilient community, supported by a united global network dedicated to human rights and lasting recovery.
እያንዳንዱ የተፈናቀለ የአማራ ተወላጅ ሰብአዊ መብቱ ተከብሮ፣ በፍትሃዊ እና በተረጋጋ ማህበረሰብ ውስጥ ህይወቱን መልሶ የሚገነባበት፣ እንዲሁም በአንድነት እና በዓለም አቀፍ የድጋፍ አውታር የታገዘ የወደፊት ተስፋ ማየት።
Core Values
Unity (አንድነት)
We believe our strength comes from standing together as one community.
ኃይላችን እንደ አንድ ማህበር በአንድነት ከመቆም እንደሚመጣ እናምናለን።
Compassion (ርህራሄ)
We serve with empathy, love, and respect for human dignity.
በርህራሄ)፣ በፍቅር እና ለሰብአዊ ክብር ተገቢውን አክብሮት በመስጠት እናገለግላለን።
Responsibility (ተጠያቂነት)
We dedicate ourselves to transparent, effective, and community-driven action.
ለግልጽነት፣ ለውጤታማነት እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ ላይ ለተመሰረተ ተግባር ራሳችንን እንሰጣለን።
Solidarity (አንድነት):
We believe in the power of a united diaspora. We stand firmly with the Amhara people, fostering a community of support that transcends borders.
የተባበረ የዳያስፖራ ኃይል ባለው ጥንካሬ እናምናለን። ድንበር ሳይገድበን ከአማራ ሕዝብ ጎን በመቆም ጠንካራ የድጋፍ አውታር እንዘረጋለን።
Human Rights & Justice (ሰብአዊ መብቶች እና ፍትህ):
We are committed to the inherent dignity of every individual and advocate for the protection of human rights and the pursuit of justice for the displaced.
ለእያንዳንዱ ግለሰብ ሰብአዊ ክብር እንቆማለን፤ ለተፈናቃዮች መብት መከበርና ለፍትህ መስፈን እንሟገታለን።
Resilience (ጽናት):
We focus not only on immediate relief but also on empowering individuals and communities to rebuild, adapt, and thrive after tragedy.
ትኩረታችን አስቸኳይ ድጋፍ መስጠት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ግለሰቦችና ማህበረሰቦች ከአደጋ በኋላ ህይወታቸውን መልሰው እንዲገነቡ፣ እንዲላመዱና እንዲበለጽጉ ማብቃት ላይ ጭምር ነው።
